Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማሳደግና ለማጠናከር ድጋፍ እያደረገ ነው – የባንኩ ፕሬዚዳንት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፉ ለማሳደግና የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለማጠናከር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ተናገሩ።

አህጉራዊ ባንኩ የኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ለማገዝ የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አንስተዋል፡፡

የግብርና ምርታማነትን ለሚያሳድጉ የአግሮ ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያና ለግብርና ምርት እሴት ልዩ ትኩረት በመስጠት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ÷ ለጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጥረት ባንኩ እየደገፈ ይገኛል ነው ያሉት።

በአፍሪካ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበ የመጣውን የግብርና ዘርፍ በመደገፍ አህጉሪቷ የምግብ ዋስትናዋን እንድታረጋግጥ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ ዘርፉም እድገት እያሳየ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቆላማ አካባቢዎች እያካሄደች የምትገኘውን የስንዴ ምርታማነት ግቡን እንዲመታም ባንኩ ድጋፍ ማድረጉንም ኢዜአ ዘግቧል።

በተለይም በተሰራጨው የተሻሻለ የስንዴ ዝርያም ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትና ምርታማነቷን በመጨመር የሚበረታታ ስራ መስራቷንም ነው ፕሬዚዳንቱ ያስረዱት።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.