Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በበርሚንግሃም የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ድል ቀንቷታል፡፡

አትሌቷ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 16 ሰከንድ 69 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈቸው፡፡

በዚህም አትሌት ጉዳፍ አዲስ ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ 9 ሰከንድ የቀራት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የተያዘ መሆኑን ከወርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.