Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር እንሠራለን – የቻይ ገንዘብ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት መሥራት እንደምትቀጥል እና ኢኮኖሚያዊ ትስስሯን ይበልጥ እንደምታጠናክር የቻይና ገንዘብ ሚኒስትር ሊዩ ኩን ገለጹ፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ ከቻይና የገንዘብ ሚኒስትር ሊዩ ኩን ጋር በቤጂንግ ተወያይቷል፡፡

ሀገራቱ የኢኮኖሚ አጋርነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ እያደረገች ላለው ጥረት ቻይና የምታደርገውን ድጋፍ አቶ አህመድ ሽዴ አድንቀዋል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የቻይና-አፍሪካ የንግድና የኢንቨስትመንት ትብብር በጋራ ጥቅምና በፖሊሲ ነፃነት ላይ የተመሠረተ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የቻይና የገንዘብ ሚኒስትር ሊዩ ኩን÷ ቻይና ከኢኮኖሚያዊ ድህነት ለመውጣት ብሎም ኢኮኖሚዋን አሳድጋ አሁን የደረሰችበት ደረጃ ለመድረስ የሄደችበትን መንገዶች ለልዑኩ አብራርተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.