Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ም/ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች በሕንድ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና የክልል ም/ቤት አፈ-ጉባኤዎች በሕንድ ያደረጉት የልምድ ልውውጥ የፓርላማ ዲፕሎማሲን ያጠናከረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የተመራ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ልዑክ በሕንድ ተጉዘው የሦስት ቀናት የልምድ ልውውጥ አድርጎ ተመልሰዋል።

በልምድ ልውውጡ የሕንድ ፓርላማ አጠቃላይ አሠራርና አደረጃጀት፣ የፓርላማ አባላት ጥያቄ አቀራረብና ሥነ-ሥርዓት፣ የፓርላማ ሥነ ምግባር፣ የህግ አወጣጥና የበጀት አወሳሰን ሥርዓት የተካተተበት ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ ፣ኤዥያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ የልምድ ልውውጡ ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፓርላማ ዲፕሎማሲ የሚያጠናክር እንደሆነ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በገጠማት ፈተና ምክንያት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ ጊዜ አጀንዳ እንድትሆን ሲደረግ ሕንድ መርህን በመከተል የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ያደረገችው ድጋፍን አስታውሰዋል ።

የሕንድ ፓርላማ የውጪ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙላሪድሃራን እንዳሉት ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣው ግንኙነት አድማሱን እንዲያሰፋ በኢኮኖሚና ፖለቲካ ዘርፎች መሰል የልምድ ልውውጦች መደረጋቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

ሕንድ በትምህርት ዘርፍ ያላትን መልካም ተሞክሮ ለኢትዮጵያ እያካፈለች ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፥ ከ1 ሺህ በላይ የሕንድ መምህራን በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስተምራሉ ብለዋል።

የኢትዮጵያና ሕንድ የሁለቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከ75 ዓመታት በላይ የተሻገርና በየጊዜው እየተጠናከረ የመጣ ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.