Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ዜጎችን ለመታደግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ዜጎችን ከሞት ለመታደግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩሉን እንዲወጣ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቀረበ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ፥ ድርቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈተና እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፥ በሀገራችንም በሰው እና በእንስሳት ህይወት ላይ አደጋ እያስከተለ ነው ብለዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ አየተከሰተ ያለውን ድርቅ በዘላቂነት ለመፍታትም እየተሰራ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ካሳለፍነው ሦሥት ተከታታይ ዓመታት እየተከሰተ ባለው ድርቅ ከ7 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ዜጎችን መታደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በድርቁ ምክንያት የሰው እና የእንስሳት ህይወት እንዳያልፍ እና ተማሪዎች ትምህርት እንዳያቋርጡ የተማሪዎች ምገባ እየተካሄደ መሆኑንም ነው ያነሱት።

በክልሉ በዚህ ዓመት ብቻ በተከሰተው ድርቅ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ነው አቶ አወሉ የገለፁት፡፡

በዚህም በክልሉ የተከሰተውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቋቋም ዳያስፖራውን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

#Ethiopia #Borena #DroughtInEthiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.