Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

አትሌቶቹ ከተሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል የ2023 የጃፓን ኦሳካ ማራቶን ውድድር ትናንት ሲካሄድ በዚህ ውድድር በሴቶች አትሌት ሄለን በቀለ እና  አትሌት በየኑ ደገፋ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት ሲያሸንፉ በወንዶች አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ አሸናፊ ሆኗል።

በሜክሲኮ በተካሄደው ጓድላሃራ የግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ በወንዶች አትሌት ያሲን ሀጂ ሲያሸንፍ በሴቶች አትሌት ሕይወት ገብረኪዳን ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቃለች።

ከትናንት በስቲያ በአሜሪካ አትላንታ ከተማ  የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር የተካሄደ ሲሆን÷ አትሌት ፀጋዬ ኪዳኑ በአንደኝነት አጠናቋል፤በሴቶች ደግሞ አትሌት ሰላም ፈጠነ ሶስተኛ ደረጃንዳድድሩን መጨረሷን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በስፔን በተደረገ የካስቴል ማራቶን ውድድር  ኢትዮጵያዊው ዳዲ ያሚ ሲያሸንፍ አትሌት ለሚ ዱሜቻ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

በተጨማሪም በጣሊያን  በተካሄደው የናፖሊ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ ያሸነፈ ሲሆን÷ እስራኤል አገር ቴላቪቭ ከተማ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ በሴቶች አትሌት ያለምጌጥ ያረጋል አሸንፋለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.