Fana: At a Speed of Life!

በተኪ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ የኦሮሚያ ክልል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሬ በሚያስቀሩ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
መንግስት ከውጭ ሀገራት በምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ለታ አበበ እንደገለጹት÷በተኪ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ባለሃብቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡
 
በተጨማሪም ባለሃብቶች በወጪ እና የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ እንደሚሰማሩ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በተለይም በውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በተከለከሉ ምርቶች ላይ ለሚሰማሩ አልሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ባለሃብቶች ከግብዓት እና መሰረተ ልማት አንጻር ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረው በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ በቅንጅት እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡
 
በክልሉ አሁን ላይ ከውጭ የሚገቡ ዘይት፣ ስኳር፣ ወተት እና መሰል ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ሃላፊው የገለጹት፡፡
 
በዚህ መሰረት በዘርፎቹ ለሚሰማሩ አልሚዎች የኢንቨስትመንት ቦታ እና ሌሎች አቅርቦቶችን በቅድሚያ እንደተዘጋጁላቸው አስረድተዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.