Fana: At a Speed of Life!

መሰረተ ልማቶች በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተሞች የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በከተማ መሰረተ ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ የ2015 ዓ.ም የከተሞች ተቋማዊ እና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስተር ጫልቱ ሳኒ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጆሃር፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታዋችና የክልልና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የዓለም ባንክ ተወካዮች ተገኝተዋል።

አውደ ጥናቱ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በዓለም ባንክ ድጋፍ (ዩ ኤል ጂ ዲ ፒ) እና ( ዩ አይ አይ ዲፒ) ፕሮግራም የተገነቡ የክልሎች የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታ ይገመገማል።

በግምገማ መድረኩ መሰረተ ልማቶች በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ መገለጹን ከድሬዳዋ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.