Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ግንባታ 78 ነጥብ 2 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም 78 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ ባለቤትነት እየተካሄደ የሚገኘው የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በመስከረም 19 ቀን 2012 ዓ.ም ስራው የተጀመረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው መጓተቱን በከተማ አስተዳደሩ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅህፈት ቤት የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ዳዊት ጥበቡ ተናግረዋል፡፡

ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የዓድዋ ድልን የሚዘክሩ ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ማካተቱ ተገልጿል።

በዚህም የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣የሲኒማ አዳራሾች፤ መዝገብ ቤት ፣ቤተ መፅሀፍት፣ የመኪና ማቆሚያ፤ የስፖርት ማዘውተሪያዎችም አካቷል።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.