Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
 
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ሲሆን በስራ ላይ ያለው ፖሊሲ ላለፉት 28 ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ከማፍራት፤ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሥራዎችን ከማበረታታት ፣ እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀቶችን መዘንጋቱ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋጥ አኳያ ሰፊ ክፍተቶች ነሩበት፡፡
በመሆኑም ለሁሉም ህጻናትና ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት ማዳረስ፤ ትውልዱን ባለብዙ ልሳን እና ተወዳዳሪ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረከት፣ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያስችል የዘርፉን ዓለም አቀፋዊ ለውጦች መሠረት ባደረገ መልኩ የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ግብ ያደረገ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምከር ቤት ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከፀደቀበት ከዛሬ ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
 
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲሆን÷ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻ ሆነው ስለአካዳሚክ ስራዎቻቸው በራሳቸው መወሰን እንዲችሉ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራ የዳበረ ዕውቀት የሚገኝባቸው ተቋማት እንዲሆኑ፣ ሕብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ የማበራዊ አገልግሎቶችን የሚያገኝባቸው፤ የራሳቸን የገቢ ምንጮች በማስፋት በሂደትም በራሳቸው በጀት የሚተዳደሩ እንዲሆኑ ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ ቀስ በቀስ በመንግስት ዩኒቨሲቲዎች ላይ የሚተገበር ረቋቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምከር ቤት ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ እዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይፀድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
 
3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ በከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት እና በማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚሰሩ የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶችን ሃላፊነት እንዲሁም ጥቅማጥቅም ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን በከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት ውስጥ በላቦራቶሪዎች፣ኢንዱስትሪዎች፣ በምርምር እና በማህረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሞያዎችን መብት እና ግዴታዎች እንዲሁም ሊሟሉላቸው የሚገቡ ጥቅሞችን በህግ መደንገግ የስራ ተነሳሽነትን የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ ለከፍተኛ ትምህርት ተልዕኮ ስኬት ድርሻው የጎላ መሆኑ ስለታመነበት ለከፍተኛ ትምህት ሁለንተናዊ እድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍየሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምር ቤት ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗ፡፡
 
4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲሆን÷ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር በእውቀት በክህሎት የጎለበተ ገበያው የሚፈልገውን የሠለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት ያደረጓቸው ጥረቶች በተግዳሮቶች የታጠሩ እና የሚጠበቀውን ውጤት ያላሳኩ በሆኑ ይህንን ትስስር በማእቀፍ ከፍ በማድረግ ከኢንዱስትሪው ጋር የሚመሰረተው ትስስር የዕውቀት ሽግግርን መሰረት ያደረገ እዲሆን፤ ለብዝሃ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ችግር ፈቺ ምርምር እንዲያከናውኑ፣ አስተማማኝ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸውና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገኙ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት መብትና ግዴታዎች መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመኘቱ ረቂቅ እዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፈው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በመሉ ድምጽ ወስኗል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.