Fana: At a Speed of Life!

የሠራተኛ ፍልሠት አስተዳደርን ለማሻሻል እየሠራሁ ነው – የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር የሰራተኛ ፍልሰት አስተዳደርን ለማሻሻል ከአጋር አካላት ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሠግድ ጌታቸው፥ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተለያዩ ሀገራት ፈልሰው ሥራ ለሚፈልጉ ሠራተኞች ጥበቃ ለማድረግ እና ከለላ ለመሥጠት ከሌሎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ፣ ከአጋር አካላት እንዲሁም ከልማት ኤጀንሲዎች ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያከናወናወናቸውን ተግባራት ዛሬ በተጀመረው ሁለተኛው የኢጋድ አባል ሀገራት የሚኒስትሮች ጉባዔ የመክፈቻ መርሐ-ግብር ላይ አቅርበዋል፡፡

የተቀናጀ የሥደተኞች አስተዳደር ÷ ስደተኞች የሚነሱበትንም ሆነ የሚሰደዱበትን ሀገር ፍልሰተኞቹን ራሳቸውን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን እንደሚጠቅም አስረድተዋል፡፡

ፍልሰተኞቹን በትክክል ማወቅ ከሀገራት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ፣ ችግር ሲደርስባቸው ለመተባበር እና ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ በሀገራቱ ፣ በቀጣናው እና በዓለምአቀፍ ደረጃ ለመውሰድ ብሎም ዕልባት ለመሥጠት ይረዳል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.