Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብስባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተጀመረው 52ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ እየተሳተፈች ነው።
 
በስብሰባው ላይ በተመድ የጄኔቫ ቢሮ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው እና የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተሳትፈዋል።
 
የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሀገራትን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት ላይ ተጨባጭ ውይይት መጀመር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
አምባሳደር ፀጋአብ በጄኔቫ የተመድ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል ታቲያና ቫሎቫያ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ማስገባታቸው ይታወቃል።
 
የምክር ቤቱ ታዛቢ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያን የወከሉት አምባሳደሩ ነገ በስብሰባው ላይ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
52ኛው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎም እንደሚጠበቅ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.