Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የቀን ማስተካከያ ተደረገባቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ እና 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል።

የፕሪሚየርሊጉ ከ14ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አክሲዮን ማህበሩ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ በ15ኛው ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ ዝናብ ሁለት ጨዋታዎች የተቋረጡ ሲሆን ጨዋታዎቹ በመጭው ማክሰኞ እና ረቡዕ እንዲካሄዱ የአክሲዮን ማህበሩ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

የ15ኛው ሳምንት የቀን ለውጥ የተደረገባቸውን ጨዋታዎች ተከትሎ የ16 እና 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች  የጨዋታ ቀን መሻሻሉን አክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.