Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የተከሰተው በረዶ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክረምቱን ወቅት ተከትሎ የተከሰተው በረዶ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በካሊፎርኒያ እና በመካከለኛው አሜሪካ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

በአውሎ ንፋሱ እና በአስጨናቂው የዓየር ፀባይ ምክንያት የኦክላሆማ፣ ካንሳስ፣ ሚዙሪ እና ቴክሳስ ነዋሪዎች በጊዜ መጠለያ እንዲፈልጉ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በርካታ ቤቶች መውደማቸው እና የኤሌክትሪክ መስመር ምሶሶዎች መውደቃቸውም ተነግሯል፡፡

120 ሺህ የሚደርሱ የሎስ አንጀለስ አካባቢ ነዋሪዎች ደግሞ ለቀናት በዘለቀ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ተመትተው የኤሌክትሪክ ኃይል ካጡ ቀናት መቆጠሩ ተገልጿል፡፡

በካሊፎርኒያ ወደ 43 ሺህ 900 ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው በዘገባው ተመላክቷል።

ኃይለኛው አውሎ ንፋስ ወደ ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ዞሮ በኔቫዳ፣ ቴክሳስ፣ ኦክላሆማ እና ሚዙሪ ተጨማሪ ጉዳት ማድረሱንና 52 ሺህ 970 ያህል ቤቶችን ከኤሌክትሪክ ኃይል ውጪ ማድረጉም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.