Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መንግስት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ለማፋጠን ቁርጠኛ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጃፓን የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ሳይዳ ሺኒቺ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እና ኢትዮጵያ አፈፃፀሙን ለማፋጠን ያላትን ቁርጠኝነት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

ከዚህ ባለፈም በመልሶ ግንባታው እና በመልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና እንድታመራ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙንም ገልጸዋል።

አምባሳደር ሳይዳ ሺኒቺ በበኩላቸው ጃፓን ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት እና የመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን እንደምትደግፍ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.