Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ34 ቢሊየን ዶላር በላይ የንብረት ውድመት መድረሱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰው ጉዳት ከ34 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚደርስ የዓለም ባንክ አስታውቋል፡፡

ይህ የጉዳት መጠን ከ2021 የቱርክ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ እድገት አራት በመቶውን ያክል እንደሚሸፍን እና የጉዳቱ የግምት መጠን የመልሶ ግንባታውን ያላካተተ መሆኑንም አመላክቷል።

ዛሬ ይፋ የሆነው የባንኩ የጉዳት ግምት ሪፖርት በሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰውን ውድመት አላከተተም።

በዓለም ባንክ የቱርክ ዳይሬክተር ሀምቤርቶ ሎፔዝ እንደገለፁት ሪፖርቱ ቱርክ ለመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ትኩረት እንድትሰጥ እና የመሬት መንቀጥቀጥን የሚቋቋሙ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እንዳለበት የሚያስጠነቅቅ ነው ብለዋል፡፡

ከንብረት ጉዳት በተጨማሪ በቱርክ በመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ በደረሰ ጉዳት 1 ነጥብ 25 ሚሊየን የሚደርሱ ቱርካውያን ለጊዜው ቤት አልባ እንደሆኑ የዓለም ባንክ መግለፁን ኤ ኤፍ ፒን ጠቅሶ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.