Fana: At a Speed of Life!

ለቦረና እርዳታያሰባሰቡ አካላት በተዘጋጁት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ገቢ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እርዳታ ያሰባሰቡ አካላት በተዘጋጁት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ገቢ እንዲያደርጉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ፡፡
 
ክልሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት÷ቦረና ዞን በድርቅ ሳቢያ የደረሰውን ጉዳት ለመቀነስ የክልሉ መንግስት ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፣ እየሰራም ይገኛም ብሏል፡፡
 
ይሁን እንጂ ለአምስት የዝናብ ወቅር ዝናብ ሳይዘንብ በመቆየቱ ለችግር የተጋለጡ ሰዎች እና እርዳታ የሚያፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ብቻ ችግሩን መፍታት አይቻልም ነው ያለው፡፡
 
ይህንኑ ምክንያት በማድረግ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ሰዎች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በድርቅ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጠው የቦረና ህዝብ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
 
ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚያስመሰግን እና በችግር ወቅት መረዳዳትና አብሮ መቆም ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ ነው ሲልም ገልጿል፡፡
 
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን ጉዳይ ለማቀናጀት ከክልል እስከ ቀበሌ ድርስ ድጋፉን የሚያስተባብር መዋቅር መዘርጋቱም ተጠቁማል፡፡
 
ክልሉ ለድጋፉ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የባንክ ሒሳብ ቁጥር መክፈቱንም አስታውቋል፡፡
 
ስለሆነም እየተሰበሰበ ያለው ድጋፍ ተጠያቂነትና ኃላፊነት ባለው መልኩ እንዲሰበሰብ ብሎም ተጋላጩ ህዝብ ጋር እንዲደርስ በተለያየ አቅጣጫ ለተጎጂው ህዝብ እያሰባሰቡ ያሉ አካላት ገንዘቡን በሚከተሉት የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች እንዲያስገቡ ተጠይቋል፡፡
 
የቡሳ ጎኖፋ የባንክ ሂሳብ ቁጥር
 
ሲንቄ ባንክ ፡ 1029565101201
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፡1000007343756
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.