Fana: At a Speed of Life!

“ግብር ለሀገር ክብር” የተሰኘ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በመጪው ሃሙስ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን “ግብር ለሀገር ክብር” የተሰኘ ሀገራዊ የታክስና የጉምሩክ ህግ ተገዢነት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ይፋ አድርገዋል።
የንቅናቄው አላማ ህገ ወጥነትን በመከላከል ገቢን ለማሳደግ ታሳቢ ደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ንቅናቄው የካቲት 23 በይፋ እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን÷ ከየካቲት እስከ የካቲት በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል ፡፡
በንቅናቄውም ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ፤ ከክልል እና ከፌደራል ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ጋር የጋራ መድረክ እንዲሁም ጉብኝቶችም እንደሚኖሩ ተገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የካቲት ወር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአፍሪካውያን ኩራት የሆነው የዓድዋ ድል በዓል የሚከበርበት በመሆኑ አባቶቻችን በዓድዋ ላይ የተቀዳጁትን ጠንካራ ኢኮኖሚ በመገንባት ከድህነት ልንላቀቅ ይገባል ፡፡
የሃገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር በመሰባሰብ ያደረግነውን አርበኝነት የአሁኑ ትውልድ በኢኮኖሚውም መድገም አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው÷ ኮሚሽኑ እራሱን በቴክኖሎጂ በማደራጀት የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆንም ግን በውስጡ ያለው ህገ ወጥነት የገቢና ወጪ ንግዱን እየጎዳው እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም በንቅናቄው ሰፊ የቁጥጥር ስራና ህገ ወጦችንም በመለየት የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል ብለዋል።
በዘመን በየነ
May be an image of 2 people, people standing, people sitting and text that says 'Mnistry of Revenue ቢዎች ሚኒ ግብር፡ ለ Maistry of Reven የገቢዎች ሚኒስ etv ያገ FANA'
All reactions:

Endale Kebede and 69 others

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.