Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የአደጋ ስጋት ደህንነት መስፈርት ያሟሉ ሆቴሎች 10 ብቻ መሆናቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከሚገኙ 180 ከሚሆኑ ባለኮከብ ሆቴሎች ዉስጥ የአደጋ ስጋት ደህንነት መስፈርት ያሟሉ ሆቴሎች 10 ብቻ መሆናቸውን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሆቴል ባለቤቶች ጋር በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ 132/2014 ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ደንቡ ተቋማት አደጋን ተከላክለው ሰላማዊና ከአደጋ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችላቸዉን መስፈርቶችን ያካተተና ደንቡን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ የተለያየ መጠን ያለው ቅጣትን የሚጥል ነው ተብሏል።

የአደጋ ስጋት ደንቡ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን÷ በደንቡ ላይ ቅሬታዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎችም ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ 180 ባለኮከብ ሆቴሎች ዉስጥ የአደጋ ስጋት ደህንነትን መስፈርትን ያሟሉ 10 ብቻ ናቸው፤በሌላ በኩልም ከ17 ሺህ 519 ተቋማት ዉስጥ ይህንኑ መስፈርት ያሟሉት 25 ብቻ ናቸው ተብሏል በውይይቱ።

በዚሁ የአደጋ ስጋት ደንብ ላይ የሚመክረው ውይይት በቀጣይ ሳምንት ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋርም እንደሚደረግ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.