Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ በግንባታ ላይ ያሉ መሰረተ ልማቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ እየተገነቡ የሚገኙ መሠረተ ልማቶች በፍጥነት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ቡድን በድሬዳዋ ከተማ በዓለም ባንክና በአስተዳደሩ የተቀናጀ በጀት በከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ መርሐ ግብር የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ መሠረተ ልማቶችን ጎብኝቷል።

ወይዘሮ ጫልቱ በዓለም ባንክ በተገኘ ብድር እና በመንግስት ተጨማሪ በጀት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኙ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዕገዛ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ÷ ፕሮጀክቶችን እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ አገልግሎት ለማስጀመር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.