Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት የ500 ቢሊየን ዩሮ የአደጋ ጊዜ መታደጊያ ማዕቀፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት የ500 ቢሊየን ዩሮ የአደጋ ጊዜ መታደጊያ ማዕቀፍ አጸደቀ።

የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ሚኒስትሮች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ለተጠቁ ሃገራት በሚውለው የአደጋ ጊዜ መታደጊያ ማዕቀፍ ላይ ተስማምተዋል።

ሚኒስትሮቹ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሮጀክት ቤት ውስጥ ለሚቀመጡ ሰራተኞች የሚውል የ200 ቢሊየን ዩሮ ዋስትናን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች ላይም ተስማምተዋል ነው የተባለው።

ስምምነቱም በአውሮፓ ህብረት ታሪክ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ኢኮኖሚያ ዊ ዕቅድ እንደሆነ ተነግሯል።

በኮሮና ቫይረስ ከአውሮፓ ሃገራት ውስጥ ስፔን እና ጣሊያን እጅግ የከፋ ጊዜን እሳለፉ ሲሆን፥ በስፔን 152 ሺህ 446 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በቫይረሱ ሳቢያም የዓለም ኢኮኖሚ እየተጎዳ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዓለም በ1930 ዎቹ  ከተከሰተው የኢኮኖሚ ድቀት ወዲህ ትልቁን የኢኮኖሚ ውድቀት ታስተናግዳለች ሲል አስጠንቅቋል።፡

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.