Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከባበርን አስመልክቶ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም በዕለቱ በምኒሊክ አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር ስነ ስርዓቱ እንደሚጀምር የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከዚያ በመቀጠል ወደ አድዋ ድልድይ የእግር ጉዞ እንደሚደረግና ዋናው ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ገልጿል፡፡

በመሆኑም በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነው የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ፣ ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣ ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡

እንዲሁም ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ፣ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ፣ ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ፣ ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ፣ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ፣ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከተጠቀሰው ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነው ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ፣ ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ፣ ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ፣ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ፣ ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ፣ ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ፣ ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ፣ ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ፣ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ፣ ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ፣ ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል፣ ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል፣ ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል፣ ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ፣ ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት፣ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ፣ በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ፣ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር፣አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር፣ ከገነት መብራት ወደ ለገሀር፣ ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ፣ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ፣ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ፣ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር ፣ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር፣ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት፣ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት፣ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)፣ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ፣ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት፣ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል፣ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎችም ይህን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለፀ ከእሮብ የካቲት 22ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የበዓሉን ድባብ ሊያደፈርሱ የሚችሉ እና ከፀጥታ ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ 987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ እንዲሰጡ ወይም በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ ኃይል መረጃውን በአካል እንዲያደርሱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.