Fana: At a Speed of Life!

ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ ድንበር አካባቢ ጥብቅ ጥበቃ እንዲደረግ አዘዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ – ዩክሬን ድንበር አካባቢ ጥብቅ የደኅንነት ቁጥጥር እና ጥበቃ እንዲደረግ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዘዙ፡፡

ፑቲን ትዕዛዝ ያስተላለፉት የዩክሬን ሰው አልባ አነስተኛ ወታደራዊ አውሮፕላን (ድሮኖች) በሀገራቱ ድንበር አካባቢ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የተፈጸሙት ጥቃቶች የጎላ ጉዳት ባያደርሱም ሞስኮ ሁኔታው እንደ ሌላ አዲስ ሥጋት ቆጥራዋለች ነው የተባለው፡፡

የሩሲያ – ዩክሬን ግጭት አንደኛ ዓመቱን ጨርሶ ሁለተኛውን ጀምሯል፡፡

ዩክሬን ለጥቃት ወደ ሞስኮ የላከችው አንድ ድሮንም ተልዕኮውን ሳይፈፅም ከዋና ከተማዋ በደቡብ ምሥራቅ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኮሎምና ወረዳ ጉስታቮ በተባለች መንደር አቅራቢያ መከስከሱ ተነግሯል፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ሌሎች ሁለት ድሮኖች መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡

ድሮኑ የተከሰከሰበት አካባቢ ግዙፉ የሩሲያ የኃይል አቅራቢ ኩባንያ ጋዝፕሮም እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.