Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በጋራ ለመስራት ምክክር ማድረጋቸውን አስታወቁ።

የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ እና የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሁለቱ ክልል አመራሮች የጋራ ስብሰባ መደረጉ ተነስቷል።

በጋራ ስብሰባውም በመልካም አስተዳደር ፣በልማት እና በመሰል ጉዳዮች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።

ክልሎቹ በጋራ ያሳኳቸውን ድሎች በማጠናከር የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ መምከራቸውን በመግለጫው አንስተዋል።

በወሰን አካባቢ ለሚያጋጥሙ ችግሮችም መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በተካሄዱ ምክክሮች መሰረት የተደረጉ ስምምነቶችን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉንም ነው ኃላፊዎች የገለጹት፡፡

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.