Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በግመሽ ዓመቱ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊውን ግብዓት እና ጥሬ እቃ እያቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ መንግስት ቅድሚያ በሰጣቸው ዘርፎች በተሰማሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለው ግብዓት በወቅቱ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ገልጿል፡፡

አዋጭ የሆኑ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በመለየት፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ ቀጣይ እና ዘላቂ የማምረትና የመሸጥ ስራቸውን በመደገፍ እየሰራ መሆኑን በድርጅቱ የፕሮጀክት ትግበራ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክተር ሱባለው መኩሪው ተናግረዋል፡፡

ጠንካራ የአቅርቦትና ግብይት ሰንሰለት በመፍጠር ጥራታቸውን የጠበቁ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን አልምቶ በማቅረብ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራትም ከኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶች ሽያጭ ና ሌሎች አገልግሎቶች 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉን ነው የተናገሩት።

በቀጣይም ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለት አሰራር እንደሚተገበር ዳይሬክተሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.