Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን በአፍሪካ ህብረት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው ሀገር በቀል የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተከበረ ነው።

ቀኑ የሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ ግዥ ስርዓትና ቀጠናዊ የአቅርቦት እሴቶችን በማሳደግ ሀገር በቀል የአፍሪካ ትምህርት ምገባን በማረጋገጥ ትምህርትን ማሻሻል በሚል መሪቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።

ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት የመጡ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፋበት የሚገኘው መድረኩ ÷የሀገር በቀል ትምህርት ምገባን በአፍሪካ ለማጠናከር የሚቻልበትን መንገድ የጠቆመ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የአፍሪካ ሀገራት የሀገር በቀል የትምህርት ምገባን ለማረጋገጥ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን መጠቀም አይነተኛ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

34 የአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ምገባ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

በሥነ – ሥርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተባበሩት መንግስታት እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.