Fana: At a Speed of Life!

የፊታችን ዓርብ ኢትዮጵያውስጥ ባሉ መስጂዶች ድጋፍ እንዲሰበሰብ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ድጋፍ የፊታችን ዓርብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መስጂዶች እንዲሰበሰብ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በሰጡት መግለጫ በቦረና በተከሰተው ድርቅ ለወገን ጥሪ ምላሽ መስጠት÷ የአንድነታችን ማሳያ የፍቅራች መግለጫ ከመሆን ባለፈ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብለዋል፡፡

በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የፊታችን ዓርብ በመላው ኢትዮጵያ ባሉ መስጂዶች ድጋፍ እንዲሰበሰብ ጥሪ የቀረበ ሲሆን÷ እዲሁም በአካባቢው ዝናብ እንዲዘንብ የፊታችን ሰኞ በሸሪዓው መሰረት ሰላት እንዲሰገድ ጥሪ ተላልፏል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሸን ባንክ፣ ዘምዘም ባንክ፣ ሂጅራ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ድጋፍ የሚደረግበት የሂሳብ ቁጥር መከፈቱ ተገልጿል፡፡

በፈቲያ አብደላ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.