Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋን የድል በዓል በአድዋ ከተማ በድምቀት እንደሚያከብሩ ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋን የድል በዓል በዓድዋ ከተማ በነገው ዕለት በድምቀት እንደሚያከብሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ የዓድዋ የድል በዓል አንድነትና አብሮነትን ለማጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ 127ኛው የዓድዋ ድል ዋዜማ ምክንያት በማድረግ የሩጫ ውድድርና የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ዓድዋ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ምልክት መሆኑን በማንሳት ፥ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሰላም ችግር ምክንያት አለመከበሩን አስታውሰዋል።

የሰላም ስምምነቱ እየተተገበረና መረጋጋት እየተመለሰ ባለበት ጊዜ የሚከበረውን የድል በዓልም ነዋሪዎቹ ልዩ እንደሆነም ነው የገለጹት።

በዓሉ በከተማዋ በነገው እለት በድምቀት እንዲከበር ቅድመ ዝግጅቶች መከናወናቸው ተነግሯል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.