Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቦረና ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለዞኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

የአየር ኃይል የሰራዊት አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማሰባሰባቸውንና ለእንስሳት መኖነት በአየር ኃይሉ ግቢ ውስጥ የተመረተ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ይልማ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ከመኖው በተጨማሪ ስንዴ እንዲሁም የእንስሳት ምግብ እንደሚገኝበትና በቀጣይ አየር ኃይሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.