Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ አንድነታችንን ማጠናከር ያስፈልጋል – አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን ጠላትን በጋራ ድል እንዳረጉት ሁሉ እኛም ያጋጠሙንን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች በመሻገር የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ አንድነታችንን ማጠናከር ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሲሉ አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የአፍሪካ የነፃነት አርማ የሆነው የአድዋ ድል በዓል በመላው የሀገራችን ህዝቦች የህይወት መስዋዕትነት የተገኘ ድል ነው ብለዋል፡፡

የአድዋ ድል የትብብር፣ የአንድነት፣ የአልበገርም ባይነት ወኔን ያነገበ፤ የድል አድራጊነት ገድል ምልክት ያስቀመጠ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ነው ሲሉም በመልዕክታቸው አንስተዋል፡፡

ጀግኖች አርበኞች እውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜትን አስቀድመው÷ በዘር፣ በብሔር፣ በሃይማኖትእና በሌሎችም ጉዳዮች ሳይከፋፈሉ በጋራ ያቆይዋትን ሀገር መጠበቅ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ምንጊዜም ለጠላቶቿ የማትንበረከክ ሀገር ናት ያሉት አቶ ርስቱ÷ አሁን ዋነኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነትን ማሸነፍ ይገባናል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.