Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር እና የሞሃመድ ስድስተኛ ፋውንዴሽን አባላት ሐረር ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዚሃ አሎዩ እና የአፍሪካ ኡለማዎች ፋውንዴሽን አባላት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሐረር ከተማ ገብተዋል።

በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር እና የሞሃመድ ስድሰተኛ ፋወንዴሽን የልዑካን ቡድን አባላት ሐረር ከተማ ሲደርሱ በሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፥ አምባሳደሯ እና የልዑካን ቡድኑ አባላት ታሪካዊ፣ የሰላምና የመቻቻል ከተማ የሆነችውን ሐረር ለመጎብኝትያሳዩትን ተነሳሽነት አደንቃለሁ ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚደረጉ ትብብሮችን ለማስቀጠል ፍላጎት እና ቁርጠኝነት እንዳለው አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.