Fana: At a Speed of Life!

በእንስሳት ልማት ግብይት ፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስርሚኒስቴር በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚተገበረው የእንስሳት ልማት ግብይት ፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ ከባንኩ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
 
በውይይት መድረኩ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ እና የዓለም ባንክ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ፕሮጀክቱን ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በጥልቀት መገምገሙን አቶ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
ባጋጠሙ የአፈፃፀም ችግሮች ዙሪያ ግልፅ የመፍትሄ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን እና በሚቀጥሉት አጭር ጊዜያት ወደ ትግበራ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.