Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት ይፋ አደረገ።

እነዚህ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የነጭ እርግብ ምልክት የተወከለ እና በአንድ ክልል መደራጀቱን አልደግፍም ለሚለው የጎጆ ምልክት ተወክሏል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባሳወቀው ውጤት መሰረትም፥

የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ እንዲደገም በመወሰኑ እና በሌሎች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ያልተካተቱ 81 የምርጫ ጣቢያዎች ሳይካተቱ፥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ መራጮች በአንድ ክልል እንደራጅ የሚለውን ምልክት መምረጣቸው ተገልጿል።

78 ሺህ 970 መራጮች ደግሞ በአንድ ክልል መደራጀቱን ያልደገፉ መራጮች መሆናቸውን ተመላክቷል።

ውጤቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ በውጤቱ ያልተካተቱ የ81 ጣቢያዎች ውጤት በዞኖቹ አጠቃላይ ውጤት ላይ ሊያመጡ የሚችሉት ተጽዕኖ ባለመኖሩ ሳይካተቱ ቀርተዋል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ሙሉ በውጤቱ ያልተካተተው በአጠቃላይ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል በመሆኑ ድጋሚ ህዝበ ውሳኔ እንደሚደረግበትም አስረድተዋል።

የምርጫ ውጤታቸው በውጤቱ ያልተካተቱት የምርጫ ጣቢያዎች የወላይታ ዞን ሙሉ በሙሉ እና ኮንሶ 4 የምርጫ ጣቢያ፣ ደቡብ ኦሞ 4 ምርጫ ጣቢያ፣ ጋሞ 21የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ጌዴኦ 23 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ጎፋ 10 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ቡርጂ ልዩ ወረዳ 2 የምርጫ ጣቢያዎች፣ አሌ ልዩ ወረዳ 3 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ አማሮ ልዩ ወረዳ 7 እና ደራሼ ልዩ ወረዳ 7 የምርጫ ጣቢያዎች ነው።

በይስማው አደራ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.