Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል ጀግኖች አያቶቻችን ያበረከቱልን የኢትዮጵያውያን የጋራ ጥሪት ነው- ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል ጀግኖች አያቶቻችን ያበረከቱልን ዘውትር የማይደበዝዝና የማይነጥፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ጥሪታችን ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የዓድዋ ድል ነጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈበት እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት ነፃነት የፀናበት የድል በዓል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዓድዋ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታሪክ እና የሕብረ ብሄራዊነት መገለጫ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ድሉ የቅኝ ግዛት ዘመን ትርክትን የቀየረ ኢትዮጵያዊውያን ገድል ነው ብለዋል።

ድሉ በዘመናዊው ዓለም የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ውስጥ በተለይም ጥቁር አፍሪካውያን  ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ መነቃቃትንና ተስፋን የሰጠ ክስተት እንደነበር አንስተዋል።

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዓሉን  ስናከብር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በልማት ስራውም በመድገም ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በዓድዋ የተገኘው አንድነት፣ጀግንነትና ጽናትም በዚህ ዘመን ትውልድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.