Fana: At a Speed of Life!

በዓድዋ ላይ ለድል አድራጊነት ያልታገለ ኢትዮጵያዊ የለም- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓድዋ ላይ በክብር ያልወደቀና ለድል አድራጊነት ያልታገለ ኢትዮጵያዊ የለም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስታላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የዓድዋ ድል የኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ድል የሆነው÷ በአፈጻጸም ብቃት የጠነከረ፣ በተሳትፎ ስፋት የተዋቀረ፣ በዓላማ ጽናት የተቀመረ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ዓድዋ የግል ክብርንና ኩርፊያን በእውነተኛ የኢትዮጵያ ፍቅር እንዲተካ ያደረገ ደማቅ ድል በመሆኑ ያኮራናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዓድዋ አስተሳስሮናል፤ አዋኅዶናል ብለዋል ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

ከዓድዋ ጀግኖች አሸናፊነታቸውን ብቻ ሳይሆን÷ ለማሸነፍ ያበቋቸውን ጉዳዮች ከመረመርናቸው ለዛሬ ማንነታችን የተሰነቁ እኛም አጉልተን ልንጠቀምባቸው የሚገቡ ትምህርቶችን እናገኝባቸዋለን ሲሉም አክለዋል፡፡

ዓድዋን ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ እንዲሁም ለመላ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት እስትንፋስ እንዲሆን ያበቃው÷ አንድነትን ከጀግንነት፤ ዓላማን ከጽናት አስተባብሮ የያዘ ምልክት በመሆኑም ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ዛሬም በዓድዋ መንፈስ ሆነን፤ በድሉ ብስራት ጠንክረን ኢትዮጵያ የምትጠብቅብንን ደማቅ ታሪክ ዳግም መስራት መቻል አለብን በማለት ነው የገለጹት፡፡

ብዙ ያልሰራነው፤ ገና ያልፈጸምነው ሥራ አለብን ያሉት ከንቲባ አዳነች÷ አየሩን በሚሞሉት አሉታዊ እሳቤዎች ወደ ኋላ እየተጓተትን የዓድዋን ፍሬ መብላት አንችልም ብለዋል፡፡

ልክ የዓድዋ ጀግኖች እንዳደረጉት ትልቁን መዳረሻችንን አልመን ለማስተካካል አብረን መቆም ይኖርብናል ብለዋ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡

#Ethiopia #Adwa #Victory

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.