Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋን የድል በዓል ስናከብር በፍቅር እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል – የሐረሪ ክልል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ጽናት፣ ክብር፣ ነፃነት፣ አንድነትና መሰል ቱሩፋቶችን ያጸና ደማቅ ታሪክ ነው ሲል የሐረሪ ክል መንግሥት ገለጸ፡፡

የድል በዓሉን ስናከብርም በእኩልነት፣ በአብሮነት፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል ብሏል የክልሉ መንግሥት፡፡

ክልሉ 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፏል፡፡

በመልዕክቱም÷የአፍሪካ የነፃነት አርማ የሆነው የዓድዋ ድል በኢትዮጵያውያን የህይወት መስዋዕትነት የተገኘ ታላቅ ድል መሆኑ ገልጿል፡፡

ጀግኖች አባቶች በዓድዋ ጦርነት የውጪ ወራሪን በድል አድራጊነት ያሸነፉት በጀግንነታቸው፣ በአንድነታቸውና በዓላማ ጽናታቸው ስለመሆኑም በመልዕክቱ ተመላክቷል፡፡

ጀግኖች አባቶች የውጪ ወራሪን አሳፍረው በመመለስ የኢትዮጵያን ክብርና ነፃነት እንዳስጠበቁ ሁሉ÷ የአሁኑ ትውልድም ኅብረ ብሔራዊ አንድነቱን በማጠናከር ሀገርን ከድህነት ነፃ ለማውጣት በጽናት ሊሠራ ይገባል ነው ያለው የክልሉ መንግሥት፡፡

በዓሉን ስናከብር ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በማጠናከር እንዲሁም እርስ በእርሳችን ያለንን አንድነት በማጎልበት መሆን አለበት ብሏል የክልሉ መንግሥት በመልዕክቱ፡፡

 

#Ethiopia #Adwa #Victory

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.