Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋውን ድል በዲፕሎማሲውም በመድገም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ማውጣት እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓድዋ ጦርነት የተገኘውን ድል በዲፕሎማሲው መስክ በመድገም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ለማውጣት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ÷ የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦችን አንገት ቀና ያደረገ፤ የቅኝ ገዥዎችን ህልም ያመከነ የጭቆና ቀንበርን የሰበረ ነው ብለዋል፡፡

የሰው ልጆችን እኩልነት በተግባር ያረጋገጠ ከኢትዮጵያ የፈነጠቀ ድል መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ÷ የዓድዋ ጀግኖች ለሀገራቸው ክብር፣ ለህዝባቸውና ባንዲራቸው ከፍታ ሲሉ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ጠላትን ድል አድርገዋል ብለዋል፡፡

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ለአፍሪካውያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ለምታደርገው ጥረት ፈር ቀዳጅ ምሳሌ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

በዓድዋ ጦርነት የተገኘውን ድል በዲፕሎማሲው መስክ በመድገም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ለማውጣት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባም ነው የሥራ ኃላፊዎቹ የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.