Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን በዘመን የማይሸረሸር ክብርን ያጸና ነው- የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ጽናት፣ በዘመን የማይሸረሸር ጀግንነት፣ ክብር፣ ነፃነት እና አንድነትን ያጸና ደማቅ ታሪክ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡

አስተዳደሩ ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ዓድዋ የአፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት ጎህ የቀደደበት መሆኑን እና በኢትዮጵያውያን ጀግኖች የህይወት መስዋዕትነት የተገኘ ታላቅ ድል መሆኑን አስተዳደሩ በመልዕክቱ አመላክቷል፡፡

ጀግኖች አባቶች በዓድዋ ጦርነት የውጭ ወራሪን በድል አድራጊነት ያሸነፉት በጀግንነታቸው፣ በአንድነታቸውና በዓላማ ጽናታቸው ነው ብሏል አስተዳደሩ፡፡

የዓድዋን የድል በዓል ስናከብር በእኩልነት፣ በአብሮነት፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ ሊሆን እንደሚገባ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.