Fana: At a Speed of Life!

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይከበራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ ይውላል፡፡

የዓድዋ ድል በዓል የዓድዋ ከተማን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሀገር የተዋደቁ ጀግኖችን እና ድሉን በሚዘክሩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ይከበራል ፡፡

በዓሉን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፥ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ላይ ብንዘዋወር በዓድዋ ጦርነት ያልተሳተፉ ቀደምቶች የበቀሉበት ምድር አይገኝም ብለዋል፡፡

ዐድዋ በችግር ተተብትቦ መቅረትን አላስተማረንም፤ ዕድልን ቆጥሮ ችግርን መሻገር እንጂ ሲሉም የእለቱን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ፥ ከትናንት ይልቅ በነገ ላይ ካተኮርን፣ ሁሉን ነገር ከኢትዮጵያ በታች ካደረግን፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ካጸናን እንደ ጉም የከበበን ፈተና ሁሉ እንደ ጢስ በንኖ ይጠፋልም ነው ያሉት።

ያኔ በድህነትና በኋላ ቀርነት ላይ፣ በመለያየትና በመከፋፈል ላይ የዐድዋ ድል ይደገማል ሲሉም ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.