Fana: At a Speed of Life!

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዓድዋ ድል በዓል የዓድዋ ከተማን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሀገር የተዋደቁ ጀግኖችን እና ድሉን በሚዘክሩ መርሐ ግብሮች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

 

በምኒሊክ አደባባይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን  አስቀምጠዋል፡፡

በመቀጠል ወደ ዓድዋ ድልድይ የእግር ጉዞ እንደሚደረግና ዋናው ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.