Fana: At a Speed of Life!

“የዓድዋን ድል በዓል ለገጠሙንና ለሚገጥሙን ችግሮች መውጫ አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል” – የትግራይ ክልል ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የዓድዋን ድል በዓል ለገጠሙንና ለሚገጥሙን ችግሮች መውጫ አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የዓድዋ ድል በዓል ከሁለት ዓመታት በኋላ ታሪክ በተፃፈበት የሶሎዳ ተራራ ግርጌ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ሲከበር አንድነትንና በጋራ መቆምን በማጉላት ሊሆን እንደሚገባ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አመላክተዋል፡፡

የዓድዋ ድል ምስጢሩ አንድነትና መተባበር መሆኑን በማንሳት አሁንም ኢትዮጵያ በጋራ መቆምን ትሻለች ነው ያሉት።

ከድሉ ኢትዮጵያዊን በአንድነት ስንቆም እንደምናሸንፍና ፈተናዎችን መወጣት እንደምንችል በመረዳት መደጋገፍ ይኖርብናል ብለዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት ብዙ ማህበራዊ ምስቅልቅሎችን የፈጠረና ሊሆን የማይገባው ነበር ያሉት የክልሉ ነዋሪዎች ፥ ከስምምነቱ ወዲህ የተገኘውን ሰላም ማፅናት ይገባልም ነው ያሉት።

በሚሰሩ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችም ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

የዓድዋ የድል በዓል ድሉ በተገኘበት ስፍራ ዛሬ በድምቀት የሚከበር ሲሆን ፥ የጎዳና ላይ ትርዒቶች፣ የኪነጥበብ ስራዎችና የተለያዩ መልዕክቶች እንደሚቀርቡ ከወጣው መርሐ-ግብር መረዳት ተችሏል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.