Fana: At a Speed of Life!

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድልድይ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድልድይ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ጀግኖች አባቶች ለዓድዋ ጦርነት ዝግጅት በማድረግ እና ለአሸናፊነት ቃል ኪዳን በመግባት የተሻገሩትን ለማስታወስ የድልድይ ማቋረጥ ትርዒት ታይቷል፡፡

ትርዒቱን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አንድ ሻንበል ጦር ያሳየ ሲሆን ፥ የዛሬው ትውልድ የአባቶችን ዓርማ አንግቦ እየሰራ የሚጓዝ መሆኑን ለማመላከት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.