Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ የድል ሁላችንም የምንኮራበት የጋራ ድላችን ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2025፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ የድል ሁላችንም የምንኮራበት የጋራ ድላችን ነው ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ሲሆን ፥ በሥነስርዓቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሥነስርዓቱ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ የዓድዋ ድል በርካቶች የተገበሩበትና የብዙሃን ዜጎች መስዋዕትነት ውጤት ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የዓድዋ ድል መላው ኢትዮጵውያን የምንኮራበት የጋራ ድል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓድዋ ድል የእኛ የታሪክ ሰሪዎች ልጆች ቀርቶ አፍሪካውያን እና ጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ነው ሲሉም ነው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተናገሩት።

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በብሄርና በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ በኢትዮጵያዊ አንድነት በጋራ በመዝመታቸው ቀኝ ገዢ ዘመናዊ ሃይል በጥቁሮች የተሸነፈበት ዘመን የማይሽረው የታሪክ ድል ነው ብለዋል፡፡

“መላው ህዝብና ሀገር ተረካቢው ትውልድም ትናንት አባቶቻችን ዛሬ ደግሞ እኛ ልጆቻቸው ያጋጠመንን ፈተናዎች ያለፍነው በፀና አንድነት ቆመን በመሆኑ ይህን በመገንዘብ ይህንኑ አንድነታችች እንድናስቀጥል እጠይቃለው “ብለዋል፡፡

የዘንድሮ በዓል ደረጃውን በሚመጥን መልኩ እንዲከበር መርሃ ግብሩን መከላከያ ሰራዊት እንዲያዘጋጅ ሃላፊነት መሠጠቱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፥ ውሳኔው ቀድም ተብሎ መደረግ የነበረበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በዚህም መከላከያ ሰራዊት በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት በዓሉ በታየው አኳኃን ማዘጋጀቱን እና ለሚቀጥሉት ዓመታትም በላቀ ደረጃ አፍሪካውያን ወንድሞችን ባሳተፈ መልኩ የአፍሪካ በዓል አድርገን በጋራ ለማክበር አቅደን እንሰራለን ሲሉን ተናግረዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.