Fana: At a Speed of Life!

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቦረና በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቦረና ዞን በደረሰው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሊቀመንበር ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲን በቦረና በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ድጋፉ እንዲደረግ በወሰኑት መሰረት ድጋፍ መደረጉን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመሆኑም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል የ10 ሚሊየን ብር እና በኦሮሚያ የንግድ ማህበረሰብ በኩል የ30 ሚሊየን ብር በድምሩ የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በቦረና እና በጉጂ ዞን ተመሳሳይ የድርቅ ችግር በተከሰተበት ወቅት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዱቄትና ለእንስሳት መኖ የሚሆን የዓይነት ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
በተመሳሳይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በቦረና ዞን በድርቅ ለተጠቁ ዜጎች 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን በቦታው ተገኝተው ያስረከቡት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ÷አሁን ለይ በዞኑ ካለው የተጎጂ ብዛት አንጻር ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ታሪኩ ለገሰ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.