Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታር የንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቤት ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታር የንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቤት ሊቀ መንበር ሼክ ካሊፍ ቢን ጃሲም ቢን ሞሃመድ አል ታንጅ ጋር በዶሃ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ባለው የኢንቨስትመንት እምቅ አቅም እና እድል ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኳታር የቢዝነስ ልዑክ አባላት በቅርቡ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.