Fana: At a Speed of Life!

በትጋት፣ በትዕግሥትና ብሔራዊ ሕጎችን በማክበር የጋራ ጥረታችን ታክሎበት ከድህነት ነጻ የሆነች ሀገር መፍጠር እንችላለን – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትጋት፣ በትዕግሥት እና ብሔራዊ ሕጎችን በማክበር የጋራ ጥረታችን ታክሎበት ከድህነት ነጻ የሆነች ሀገር መፍጠር እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የተዘጋጀውን የታክስ እና የጉምሩክ ሕግ ተገዥነት ሀገራዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ግዴታቸውን በእውነት ሲወጡ ለነበሩ ግብር ከፋዮች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ንቅናቄው ዜጎች በግብርና ጉምሩክ የተቋቋሙትን ሕግ እና መመሪያዎች እንዲያከብሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ከድህነት መውጣት የምንችለው በተባበረ ክንዳችን ሃብቶችን በመጠቀም ማልማት ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በአድዋ ድል ያሳየነውን አይበገሬነት በተባበረ ክንዳችን አቅማችንን በመጠቀም የተሻለች ሀገር ለመገንባት መሥራት አለብን ብለዋል።

የችግሮች ሁሉ መንስኤ የሆነውን የድህነት ቀንበር ለመስበርም በጋራና በትብብር በትጋት ልንሰራ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የጋራ ሃብቶችን ተጠቅሞ በጋራ ለመልማት ብዙ ጉድለቶች አሉብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያ የተሟላ ክብርና ነፃነት እንዲኖራት የራሷን ወጪ በራሷ አቅም መሸፈን አለባት ብለዋል።

ኢትዮጵያ የእዳ ጫና ያጎበጣት መሆኑን ጠቅሰው÷ እዳዋን በማቃለል የተሟላ ነፃነቷን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.