Fana: At a Speed of Life!

የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ይቀርፋል የተባለ የጥቆማ መስጫ ሶፍትዌር ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችንይቀርፋል የተባለ የጥቆማ መስጫ ሶፍትዌር ማበልጸጉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ሶፍትዌር÷ ዜጎች በየተቋማቱ አገልግሎት ለማግኘት ሄደው ለብልሹ አሰራር ሲጋለጡ እንዲሁም የሙስና ተግባር ሲያጋጥማቸው በስልካቸው ጥቆማ የሚሰጡበት የቴክኖሎጂ ነው ተብሏል።

በዚህም ማንኛውም ጥቆማ ሰጪ ያለምንም ስጋት ከኢንተርኔት ጋር ስልኩን በማገናኘት የሚስተዋሉ የብልሹ እና የሙስና ተግባራትን መጠቆም እንደሚያስችለው የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ አብራርተዋል።

ይህ የቴክኖሎጂ ስርዓት ደህንነቱ 24 ሰዓት የተጠበቀ መሆኑን ነውዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር እና የሙስና ወንጀል ለመቅረፍ ዜጎች በዚህ ቴክኖሎጂ ጥቆማ በመስጠት ርብርብ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ዛሬ ይፋ የተደረገው የጥቆማ መስጫ ሶፍትዌር ርክክብ ተደርጓል።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ መካከል የውል ስምምነት ፊርማ መከናወኑ ተጠቁሟል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.