Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች የማስተላለፍ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 420 የሚደርሱ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች የማስረከብ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል መንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
ትራክተሮቹ ለአርሶ አደሮች በቀረበው 20 በ80 የቁጠባ ሥርዓት ከባንክ ጋር በማስተሳሰር የቀረቡ መሆናቸውን ቢሮው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡
 
ትራክተሮቹ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ እና የእርሻ ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የተሰሩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.