Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ 100 ተማሪዎች የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና አቅም ለሌላቸው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ 100 ተማሪዎች የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ።

በድርቁ አስከፊ ችግር ውስጥ ሆነው ለከፍተኛ ትምህርት ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በአቅም ማነስ መቅረት የለባቸውም በሚል በአካባቢው ተወላጆችና ነዋሪ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ዶክተር ጎዳና ጃርሶ፣ዶክተር ሳምሶን እሸቱ እንዲሁም ጓደኞቻቸው አማካኝነት ነው ድጋፉ የተደረገው።

ለ100 ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ ለአሁኑ ወደ ዩኒቨርሲቲ መሄጃ እንዲሆናቸው ሲሆን፥ በቀጣይነት ትምህርታቸውን እስከሚያጠናቅቁ ድጋፉ ይቀጥላል ተብሏል።

ተጨማሪ 100 ተማሪዎችም በተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የድጋፉ አስተባባሪ አካል የሆኑት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ ተናግረዋል።

ይህ ድጋፍ በትምህርታቸው ላይ የስነ ልቦና ጉዳት እንዳይደርስባቸው ብርታት ለመሆን የታሰበ መሆኑንም ነው የገለፁት።

ትምህርት ለሁሉም መሰረት ነው ሲሉ በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተማረ የሰው ሀይል መፍጠር ወሳኝ ነው መሆኑን ገልፀዋል።

ለዚህ ደግሞ ሁሉም በድርቁ ለተጎዱት በተለይም ለተማሪዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.