Fana: At a Speed of Life!

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተከናወኑ የ90 ቀን ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ የ90 ቀን ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

የዳቦ ፋብሪካ፣ የምገባ ማዕከል፣ የከብት እርባታ ክላስተር ማዕከል፣ የዶሮ እርባታ ክላስተር ማዕከል፣ ሞዴል የከተማ ግብርና እንዲሁም ሞዴል መንደሮች ፕሮጀክቶች ናቸው ስራ የጀመሩት፡፡

ፕሮጀክቶቹ የሕዝቡን የኑሮ ውድነት እና ጫና በተግባር የሚያቃልሉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

“ስራው የነዋሪዎችን ችግሮች ደጋግመን በማውራት የኑሮ ጫናን እንደማንለውጥ፣ ይልቁኑም ከችግሮቹ እንደምናሻገረው አምነን የመረጠንን ህዝብ ዝቅ ብለን በማገልገል ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ያረጋገጠልን ነው”ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.